-
-
Amharic (NT)
-
-
27
|Lucas 19:27|
ነገር ግን እነዚያን በላያቸው ልነግሥ ያልወደዱትን ጠላቶቼን ወደዚህ አምጡአቸው በፊቴም እረዱአቸው።
-
28
|Lucas 19:28|
ይህንም ከተናገረ በኋላ፥ ወደ ኢየሩሳሌም ሲወጣ ይቀድማቸው ነበር።
-
29
|Lucas 19:29|
ደብረ ዘይትም በሚባል ተራራ አጠገብ ወዳሉት ወደ ቤተ ፋጌና ወደ ቢታንያ በቀረበ ጊዜ፥ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለቱን ላከና።
-
30
|Lucas 19:30|
በፊታችሁ ወዳለችው መንደር ሂዱ፥ ወደ እርስዋም ገብታችሁ ከሰው ማንም ገና ያልተቀመጠበት ውርንጫ ታስሮ ታገኛላችሁ፥ ፈትታችሁም አምጡት።
-
31
|Lucas 19:31|
ማንም። ስለ ምን ትፈቱታላችሁ? ብሎ ቢጠይቃችሁ፥ እንዲሁ። ለጌታ ያስፈልገዋል በሉ አላቸው።
-
32
|Lucas 19:32|
የተላኩትም ሄደው እንዳላቸው አገኙ።
-
33
|Lucas 19:33|
እነርሱም ውርንጫውን ሲፈቱ ጌቶቹ። ውርንጫውን ስለ ምን ትፈቱታላችሁ? አሉአቸውም
-
34
|Lucas 19:34|
እነርሱም። ለጌታ ያስፈልገዋል አሉ።
-
35
|Lucas 19:35|
ወደ ኢየሱስም አመጡት፥ በውርንጫውም ላይ ልብሳቸውን ጭነው ኢየሱስን አስቀመጡት።
-
36
|Lucas 19:36|
ሲሄድም ልብሳቸውን በመንገድ ያነጥፉ ነበር።
-
-
Sugerencias
Haga clic para leer Números 33-34