-
-
Amharic (NT)
-
-
39
|Lucas 18:39|
በስተ ፊት ይሄዱ የነበሩትም ዝም እንዲል ገሠጹት፤ እርሱ ግን። የዳዊት ልጅ ሆይ፥ ማረኝ እያለ አብዝቶ ጮኸ።
-
40
|Lucas 18:40|
ኢየሱስም ቆሞ ወደ እርሱ እንዲያመጡት አዘዘ። በቀረበም ጊዜ። ምን ላደርግልህ ትወዳለህ? ብሎ ጠየቀው።
-
41
|Lucas 18:41|
እርሱም። ጌታ ሆይ፥ አይ ዘንድ ነው አለው።
-
42
|Lucas 18:42|
ኢየሱስም። እይ፤ እምነትህ አድኖሃል አለው።
-
43
|Lucas 18:43|
በዚያን ጊዜም አየ፥ እግዚአብሔንም እያከበረ ተከተለው። ሕዝቡም ሁሉ አይተው እግዚአብሔርን አመሰገኑ።
-
1
|Lucas 19:1|
ወደ ኢያሪኮም ገብቶ ያልፍ ነበር። እነሆም ዘኬዎስ የሚባል ሰው፥ እርሱም የቀራጮች አለቃ ነበረ፥ ባለ ጠጋም ነበረ።
-
3
|Lucas 19:3|
ኢየሱስንም የትኛው እንደ ሆነ ሊያይ ይፈልግ ነበር፤ ቁመቱም አጭር ነበረና ስለ ሕዝቡ ብዛት አቃተው።
-
4
|Lucas 19:4|
በዚያችም መንገድ ያልፍ ዘንድ አለውና ያየው ዘንድ ወደ ፊት ሮጦ በአንድ ሾላ ላይ ወጣ።
-
5
|Lucas 19:5|
ኢየሱስም ወደዚያ ስፍራ በደረሰ ጊዜ፥ አሻቅቦ አየና። ዘኬዎስ ሆይ፥ ዛሬ በቤትህ እውል ዘንድ ይገባኛልና ፈጥነህ ውረድ አለው።
-
6
|Lucas 19:6|
ፈጥኖም ወረደ በደስታም ተቀበለው።
-
-
Sugerencias
Haga clic para leer Números 33-34