- 
			
				
- 
									
   Amharic (NT)									 - 
									
									 
- 
									
									1
									 
									 
									|1 Corintios 16:1|
									ለቅዱሳንም ገንዘብን ስለ ማዋጣት፥ ለገላትያ አብያተ ክርስቲያናት እንደ ደነገግሁት እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉ።									
									    
								 
- 
									
									2
									 
									 
									|1 Corintios 16:2|
									እኔ ስመጣ ይህ የገንዘብ ማዋጣት ያን ጊዜ እንዳይሆን፥ ከእናንተ እያንዳንዱ በየሳምንቱ በፊተኛው ቀን እንደ ቀናው መጠን እያስቀረ በቤቱ ያስቀምጥ።									
									    
								 
- 
									
									3
									 
									 
									|1 Corintios 16:3|
									ስመጣም ማናቸውም ቢሆኑ የታመኑ የሚመስሉአችሁ ሰዎች ቸርነታችሁን ወደ ኢየሩሳሌም ያደርሱ ዘንድ ደብዳቤ ሰጥቼ እልካቸዋለሁ፤									
									    
								 
- 
									
									4
									 
									 
									|1 Corintios 16:4|
									እኔ ደግሞ ልሄድ የሚገባኝ ብሆን ከእኔ ጋር አብረው ይሄዳሉ።									
									    
								 
- 
									
									5
									 
									 
									|1 Corintios 16:5|
									በመቄዶንያም ሳልፍ ወደ እናንተ እመጣለሁ፤ በመቄዶንያ አድርጌ አልፋለሁና፤									
									    
								 
- 
									
									6
									 
									 
									|1 Corintios 16:6|
									እናንተም ወደምሄድበት ወደ ማናቸውም ስፍራ በጉዞዬ እንድትረዱኝ ምናልባት በእናንተ ዘንድ እቆይ ወይም እከርም ይሆናል።									
									    
								 
- 
									
									7
									 
									 
									|1 Corintios 16:7|
									አሁን እግረ መንገዴን ሳልፍ ልጎበኛችሁ አልወድምና፤ ጌታ ቢፈቅደው የሆነውን ዘመን በእናንተ ዘንድ ልሰነብት ተስፋ አደርጋለሁና።									
									    
								 
- 
									
									8
									 
									 
									|1 Corintios 16:8|
									በኤፌሶን ግን እስከ በዓለ ኀምሳ ድረስ እሰነብታለሁ።									
									    
								 
- 
									
									9
									 
									 
									|1 Corintios 16:9|
									ሥራ የሞላበት ትልቅ በር ተከፍቶልኛልና ተቃዋሚዎችም ብዙ ናቸው።									
									    
								 
- 
									
									10
									 
									 
									|1 Corintios 16:10|
									ጢሞቴዎስም የመጣ እንደ ሆነ በእናንተ ዘንድ ያለ ፍርሃት እንዲኖር ተጠንቀቁ፤ እንደ እኔ ደግሞ የጌታን ሥራ ይሠራልና፤ እንግዲህ ማንም አይናቀው።									
									    
								 
 - 
									
 - 
				
Sugerencias
 

Haga clic para leer Juan 16-18